ቢያበሉኝ ቢያጠጡኝ

ቢያበሉኝ ቢያጠጡኝ
ፈትፍተው ቢያጎርሱኝ
ያሻኸውን ውሰድ
ኹሉ ያንተ ነው ቢሉኝ
እኔስ እንደስሟ የጣፈጠ አጣሁኝ
አዝ---------------------//
የዚህ ዓለም ነገር ባዶ ሆኖብኛል
ዛሬ የበላሁት ነገ ይርበኛል
መራራው ሕይወቴ ጣፋጭ የሚሆነው
እመቤቴ ስሚኝ በአንቺ ጨውነት ነው
አዛኝቷ ስሚኝ በአንቺ ጨውነት ነው
አዝ---------------------//
አንቺ የሌለሽበት ማዕዴ ባዶ ነው
ስምሽን ካልጠራሁ ጣፋጭ መራራ ነው
በእጄ ከጨበጥኩት የመሶብ እንጀራ
ማርያም የሚለው ስም ጣፋጭ ነው ሲበላ
አዝ---------------------//
ተስፋ ያደረገው አንቺን በሕይወቱ
ስለሆንሽለት ነው ለተማሪ ራቱ
እኔም እልሻለሁ የኑሮ ጣዕሜ
ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገሪያዬ
← መዝሙር