ቡሄ በሉ
✦
ቡሄ በሉ ሆ ፪
ልጆች ሀሉ ሆ
ልጆች ሀሉ ሆ
የእኛማ ጌታ የዓለም ፈጣሪ
የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሐሪ
በደብረታቦር የ ተገ
ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ የታየ ው
ልብሱ እንደ ብርሃን ያንፀባረቀው
የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሐሪ
በደብረታቦር የ ተገ
ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ የታየ ው
ልብሱ እንደ ብርሃን ያንፀባረቀው
ድመፅህን ሰማና በብሩህ ደመና
የቡሄው ብርሃን ለእኛ መጣልን
የቡሄው ብርሃን ለእኛ መጣልን
ያዕቆብ ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ
አምላክን አዩት ሙሴ ኤሊያስ
አባትም አለ ልጄን ስሙ
ቃል ነውና የወለድኩት
አምላክን አዩት ሙሴ ኤሊያስ
አባትም አለ ልጄን ስሙ
ቃል ነውና የወለድኩት
ታቦር አርሚየም ብርሃን ታየባቸው
በቅዱስ ተራራ በጣም ደስ አላቸው
ሰላም ሰላም የታቦር ተራራ
ብርሃነ መለኮት በአንቺ ላይ አበራ
በቅዱስ ተራራ በጣም ደስ አላቸው
ሰላም ሰላም የታቦር ተራራ
ብርሃነ መለኮት በአንቺ ላይ አበራ
በተዋህዶ ወልድ የከበረው
የእግዚአብሄር አብ ልጅ ወልደ ማርያም ነው
ቡሄ በሉ፪ የአዳም ልጆች ብርሃንን ተቀበሉ
የእግዚአብሄር አብ ልጅ ወልደ ማርያም ነው
ቡሄ በሉ፪ የአዳም ልጆች ብርሃንን ተቀበሉ
አዝ
አባቴ ቤት አልኝ ለከት
እናቴም ቤት አልኝ ለከት
እጎቴም ቤት አልኝ ለከት
አክስቴም ቤት አልኝ ለከት
ተከምሯል እንደ ኩበት
እናቴም ቤት አልኝ ለከት
እጎቴም ቤት አልኝ ለከት
አክስቴም ቤት አልኝ ለከት
ተከምሯል እንደ ኩበት
የዓመት ልማችን ከጥንት የመጣ
ከተከመረው ከመሶብ ይወጣ
ከደብታቦር ጌታ ስለመጣ
የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ
ከተከመረው ከመሶብ ይወጣ
ከደብታቦር ጌታ ስለመጣ
የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ
ኢትጵያውያን ታሪክ ያላችሁ
ባህላችሁን ያዙ አጥብቃችሁ
ችቦውን አብሩት አንደ አባቶቻችሁ
ምሥጢር ስላለው ደስ ይበላችሁ
ባህላችሁን ያዙ አጥብቃችሁ
ችቦውን አብሩት አንደ አባቶቻችሁ
ምሥጢር ስላለው ደስ ይበላችሁ
አባቶቻችን ያወረሱን
የቡሄን
የቡሄን
ትርጉም ፡ - ያሳውቁን
እንድንጠብቀው ለእኛ የሰጡን
ይህን ነውና ያስረከቡን
ለድንግል ማርያም አስራት የሆንሽ
ቅዱሳን ጻድቃን የሞሉብሽ
በረከታቸው ያደረብሽ
ሁሌም እንግዶች የሚያርፉብሽ
ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ነሽ
ቅዱሳን ጻድቃን የሞሉብሽ
በረከታቸው ያደረብሽ
ሁሌም እንግዶች የሚያርፉብሽ
ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ነሽ
ለሐዋርያት የላከ መን ፈስ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ፀጋውን ያፍስስ
በሥነ ምግባር እንድንታደስ
በቅን ልቡና በጥሩ መንፈስ
በረከተ በሄ ለሁላችን ይድረስ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ፀጋውን ያፍስስ
በሥነ ምግባር እንድንታደስ
በቅን ልቡና በጥሩ መንፈስ
በረከተ በሄ ለሁላችን ይድረስ
ዓመት አውደ ዓመት ድገምና
በጋሽዬ ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ያወርድ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገምና እመ ድገምና
በእምዬ ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ይግባ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
ማርና ወተት ድገምና ዓመት ድገምና
ይትረፍረፍ በእወነት ድገምና ድገምና ድገምና
በጋሽዬ ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ያወርድ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገምና እመ ድገምና
በእምዬ ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ይግባ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
ማርና ወተት ድገምና ዓመት ድገምና
ይትረፍረፍ በእወነት ድገምና ድገምና ድገምና
✦