ቸርነትህ ብዙ

ቸርነትህ ብዙ ምሕረትህ ብዙ
በጉዞአችን ርዳን ጠባብ ነው መንገዱ
ድንቅ ነው አምላክ ሆይ ፍቅርህ
ለኛ ድንቅ ነው ለኛ
አንተ ነህ መልካም እረኛ
እስራኤል ወደቀ እስራኤል ተነሣ
መንገድ አልቀናውም አምላኩን ቢረሣ
የያእቆብን አምላክ እግዚአብሔርን ይዞ
ምን እንዳተረፈ አውቆታል በጎዞ
አዝ ---
መንገዱ አይታክትም ጎዳናው የቀና እግዚአብሔር ከፊትም ከኋላም አለና
እርሱ የሌለበት ቢመችም መንገዱ
አቅጣጫው ወደ ሞት አይቀርም መውሰዱ
አዝ ---
በመንገድ ዝለን ወድቀን መቼ ቀርተናል
የያእቆብ አምላክ ደግፎ አንስቶናል
እግዚአብሔር ሲጠራን በቀደመው መንገድ
ጉዞአችን ወዴት ነው በሞት ለመወሰድ
አዝ ---
አምላክ ሆይ ፍቅርህን በልባችን ሣለው
እስከ ሞት በመስቀል የወደደን ማነው
በበረሃው ጽናት ቢጸናብን ረሀቡ
በረከት ሞላኸን ተረፈልን ምግቡ
አዝ ---
← መዝሙር