ቸሩ ሆይ

ቸሩ ሆይ ለእኛ ብለህ ተሰቀልክ ወይ
ሔዋን ብትበድል እንዲህ እንደዋዛ
መጣ ተሰቀለ የዓለሙ ቤዛ
የተከሰሰበት ወንጀሉ ቢወራ
ለምጽ ስላነጻዕውር ስላበራ
አንካሳን ማዳኑ ማቅናት ጎባጣውን
ለፍርድ አቀረቡት እውነት የሠራውን
ባህልን ለውጧል ሰንበትንም ሽሯል
ይህ በደለኛ ነው መሞት ይገባዋል
ብለው ስለአወጁ ባንድነት ሁሉም
ለእኛ ተሰቀለ መድኃኔዓለም
ዘማሪ ሲራክ ታደሰ
← መዝሙር