ችርነተህ ነወ
✦
ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከዛሬ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ /ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ/2 ፪
አዝ.........................
መክሊቴንም ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እንዳትረሳኝ
በፍቅር ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በረሐብ በእርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ አምላኬ እንድትምረኝ
ለይቅርታ መጣሁ ይቅር በለኝ
አዝ.......................
አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ
ባንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታ ለባርያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር
ስራህን ለትውልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብዬ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ
አዝ..................
በሰው እጅ መመካት አቁሚያለሁ
ረዳቴ አንተ ነህ አውቂያለሁ
አንተ ከጠበከኝ በሕይወቴ
ቅጥሬ አይደፈርም መድኃኒቴ
የኔን ስራ ተወው ተግባሬንም
የመስቀሉን ነገር መርሳቴንም
አዚሜን አንሰተህ አንተን ልይህ
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ /ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ/2 ፪
አዝ.........................
መክሊቴንም ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እንዳትረሳኝ
በፍቅር ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በረሐብ በእርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ አምላኬ እንድትምረኝ
ለይቅርታ መጣሁ ይቅር በለኝ
አዝ.......................
አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ
ባንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታ ለባርያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር
ስራህን ለትውልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብዬ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ
አዝ..................
በሰው እጅ መመካት አቁሚያለሁ
ረዳቴ አንተ ነህ አውቂያለሁ
አንተ ከጠበከኝ በሕይወቴ
ቅጥሬ አይደፈርም መድኃኒቴ
የኔን ስራ ተወው ተግባሬንም
የመስቀሉን ነገር መርሳቴንም
አዚሜን አንሰተህ አንተን ልይህ
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ
✦