ዴማስ ሆይ ተመለስ

የይሁዳ ጉካ አያዋጣምና
ዴማስ ወደ ሕይወት እባክህ ቶሎ ና
ከወንጌል ገበ መመገብ ጀምረህ
ወንድሜ ተመለስ ወዴት ትሄዳለህ
ይጠራሃልና መስቀሉን ተመልከት
የወንጌል ቡቃያ እውነተኛ ሕይወት
አዝ . . .
ብዙ ክርስቲያኖች መንገዱን ጀምረው
የዓለም አሸንክ ብ ድምቀት ሲጠራቸው
ፈተና ሲመጣ ወንጌሉን ወርውረው
ሞትን ይመርጣሉ ሕይወትን ሰርዘው
አዝ . . .
የመስቀሉ ሕይወት ከልብህ ሳይጠፋ
በእግዚአብሔር ጉባኤ መስክረህ በይፋ
ልጄ የተባልከው በጥምቀት ቀለበት
እንዴት ትሄዳለህ ተነድተህ ወደሞት
አዝ . . .
የክብር አክሊሉ ተዘጋጅቶልሃል
አምላክ ለሽልማት ዴማስ ሆይ ይልሃል
ወዴት ትሄዳለህ እባክህ ተመቀስ
← መዝሙር