ደመቀ አበራልን
✦
ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
በቤተክርስቲያን ጥላ ተከልለው
ተክሊል አድርገዋል ሙሽሪት ሙሽራው
ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ስለተሰጣቸው
ሙሽሪት ሙሽራው አበራ ገፃቸው
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
በቤተክርስቲያን ጥላ ተከልለው
ተክሊል አድርገዋል ሙሽሪት ሙሽራው
ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ስለተሰጣቸው
ሙሽሪት ሙሽራው አበራ ገፃቸው
ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
የተራራቀ አካል አንድ ሆነ በተክሊል
እግዚአብሔር ይመስገን እልል፪ እንበል
አጥንትሽ ከአጥንቴ ሥጋሽ ከሥጋዬ
አዳም የሰበከው ይኸው ዛሬ ታዬ
እግዚአብሔር ይመስገን እልል፪ እንበል
አጥንትሽ ከአጥንቴ ሥጋሽ ከሥጋዬ
አዳም የሰበከው ይኸው ዛሬ ታዬ
ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
የተክሊሊ ብርሃኗ በእኛ መሀል በርቶ
ረቂቅ አንድነት ታየ በእርስዋ ጐልቶ
ይህን ድንቅ ነገር ለማየት ያበቃን
ምሥጢሩን የሚገልጽ እግዚአብሔር ይመስገን
ረቂቅ አንድነት ታየ በእርስዋ ጐልቶ
ይህን ድንቅ ነገር ለማየት ያበቃን
ምሥጢሩን የሚገልጽ እግዚአብሔር ይመስገን
ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
ነጭ መጐናጸፊያ በአንድ ተጐናጽፈው
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አረፈ በጥላው
ሙሽሪት ሙሽራው ለፍቅር ተሸነፉ
ለቁርባን መቁረቢያ ነጭ ልብስ አሰፉ
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አረፈ በጥላው
ሙሽሪት ሙሽራው ለፍቅር ተሸነፉ
ለቁርባን መቁረቢያ ነጭ ልብስ አሰፉ
ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
✦