ድንገል ሆይ
✦
ወላዲተ አምላክ የሁሉ እመቤት
ለምኝልን ለእኛ ከልጅሽ ምሕረት
በአንቺ አማላጅነት በእርሱ ቸርነት
እንዲያወጣን ነጻ ከፍርድ ቅጣት
ድንግል ሆይ ለምኝልን ፪
በበደል ተዳክሞ ፈቃደ ነፍሳችን
በምድራዊ ምኞት ናዉዞ ልቦናችን
ፍቅርና ትሕትና ጠፍቶ ከፊታችን
ለሞት እንዳይሰጠን ይህ ክፉ ሥራችን
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የምስኪኖች ተስፋ የደካሞች ኃይል
ጠዉልገናልና ጥላ ሁኚን ድንግል
እምነት ጨምሪልን ልቦናችን ይጽና
እመአምላክ አብሪልን የመዳንን ፋና
አዝ ፥፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ፍጹም እንዳናዝን እንዳናፍር ኋላ
ተነጥቀን እንዳንቀር ከዘለዓለም ተድላ
በፍቅርሽ መልሺን ከሲኦል ጎዳና
ድንግል መመኪያችን ተስፋችን ነሽና
ለምኝልን ለእኛ ከልጅሽ ምሕረት
በአንቺ አማላጅነት በእርሱ ቸርነት
እንዲያወጣን ነጻ ከፍርድ ቅጣት
ድንግል ሆይ ለምኝልን ፪
በበደል ተዳክሞ ፈቃደ ነፍሳችን
በምድራዊ ምኞት ናዉዞ ልቦናችን
ፍቅርና ትሕትና ጠፍቶ ከፊታችን
ለሞት እንዳይሰጠን ይህ ክፉ ሥራችን
አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
የምስኪኖች ተስፋ የደካሞች ኃይል
ጠዉልገናልና ጥላ ሁኚን ድንግል
እምነት ጨምሪልን ልቦናችን ይጽና
እመአምላክ አብሪልን የመዳንን ፋና
አዝ ፥፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥
ፍጹም እንዳናዝን እንዳናፍር ኋላ
ተነጥቀን እንዳንቀር ከዘለዓለም ተድላ
በፍቅርሽ መልሺን ከሲኦል ጎዳና
ድንግል መመኪያችን ተስፋችን ነሽና
✦