ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
✦
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
ሊቀ መዘ.ቴድሮስ ዮሴፍ
================
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀለለችው
የለምና ሥፍራ ለእንግዶች ማረፊያ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደሪያ
አ.ዝ---------------------------//
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ የምስራች ሊያወራ
የሕፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር ፪
አ.ዝ---------------------------//
ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤወን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ለዓለም ተናገሩ ንጉሥ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር ፪
አ.ዝ---------------------------//
የይሁዳ ምድር ምስጋናን ተሞላ
ንጉሥ መጥቷል እና ከናዘሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተለሔም ታውራ
ዝማሬ ሲውጣት ተረስቶ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር ፪
አ.ዝ---------------------------//
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ እንደ ሰው
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለው
ገረማት ጥበቡ ታናሿን ሙሽራ
ተዋህዷል እና ቃል ከሥጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር ፪
ሊቀ መዘ.ቴድሮስ ዮሴፍ
================
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀለለችው
የለምና ሥፍራ ለእንግዶች ማረፊያ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደሪያ
አ.ዝ---------------------------//
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ የምስራች ሊያወራ
የሕፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር ፪
አ.ዝ---------------------------//
ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤወን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ለዓለም ተናገሩ ንጉሥ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር ፪
አ.ዝ---------------------------//
የይሁዳ ምድር ምስጋናን ተሞላ
ንጉሥ መጥቷል እና ከናዘሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተለሔም ታውራ
ዝማሬ ሲውጣት ተረስቶ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር ፪
አ.ዝ---------------------------//
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ እንደ ሰው
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለው
ገረማት ጥበቡ ታናሿን ሙሽራ
ተዋህዷል እና ቃል ከሥጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር ፪
✦