ድንግል ሆይ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ
✦
ድንግል ሆይ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል
እመቤቴ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል
ደካማ ነኝ እኔ ምግባር ይጎድለኛል፪
እመቤቴ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል
ደካማ ነኝ እኔ ምግባር ይጎድለኛል፪
በሥጋዊ ሳይሆን በመንፈስ ዐይኖቼ
ለማየት እሻለሁ ከልቤ ጓጉቼ
ሥራዬ የከፋ መሆኑን አውቃለሁ
ስምሽንም መጥራት እጅግ እፈራለሁ
ለማየት እሻለሁ ከልቤ ጓጉቼ
ሥራዬ የከፋ መሆኑን አውቃለሁ
ስምሽንም መጥራት እጅግ እፈራለሁ
ክብርሽ የበዛ ነው ቤዛዊተ ኵሉ
ምሕረት ታሰጫለሽ ላመነብሽ ሁሉ
ባንቺ የተመካ ምንም አያገኘው
የገሃነም እሳት ሲዖልም አይነካው
ምሕረት ታሰጫለሽ ላመነብሽ ሁሉ
ባንቺ የተመካ ምንም አያገኘው
የገሃነም እሳት ሲዖልም አይነካው
የልዑል ማደሪያ የሲና ዕፀ ጳጦስ
አንቺን ላመስግንሽ ከደዌ እንድፈወስ
ፍቀጂልኝ ድንግል ካንቺ ጋር እንድኖር
ልጅሽን ማልጂልኝ እንዲያበቃን ለክብር
አንቺን ላመስግንሽ ከደዌ እንድፈወስ
ፍቀጂልኝ ድንግል ካንቺ ጋር እንድኖር
ልጅሽን ማልጂልኝ እንዲያበቃን ለክብር
ምንም ተስፋ የለኝ ያላንቺ እናቴ
እመካብሻለሁ እስከ ዕለተ ሞቴ
የምስኪኖች አጽናኝ የጭንቅ ቀን ደራሽ
የልቤ ማረፊያ ምግብ መጠጤ ነሽ
እመካብሻለሁ እስከ ዕለተ ሞቴ
የምስኪኖች አጽናኝ የጭንቅ ቀን ደራሽ
የልቤ ማረፊያ ምግብ መጠጤ ነሽ
የጌታዬ እናት ድንግል እመቤቴ
ተወስና ትኑር ካንቺ ዘንድ ሕይወቴ
የትኅትና ምንጭ የፍቅር ውቅያኖስ
ጠጥቼ ልርካብሸ ድንግል እንድፈወስ
ተወስና ትኑር ካንቺ ዘንድ ሕይወቴ
የትኅትና ምንጭ የፍቅር ውቅያኖስ
ጠጥቼ ልርካብሸ ድንግል እንድፈወስ
✦