ድንግል መከራሽን

ድንግል መከራሽን ጥቂት ላስሰው
በሄሮድስ ዘመን ፍጥረት ያለቀሰው
አንቺ የአምላክ እናት ደግሞም እመቤት
እንደ ችግረኛ ተነሳሽ ስደት
ኸረ ለመሆኑ እንዴት አለቀልሽ
ስትንከራተቺ በረሃን አቆርጠሸ
ይገሉታል ብለሽ ለልጅሽ አስበሽ
በሔሮድስ ዘመን መከራሽን አየሽ
አዛኝቷ ማርያም በጠራሁሽ ጊዜ
እንድትደርሽልኝ በመከራ ጊዜ
መከራን ያየ ሰው መቸም አይጨክንም
አትጨክኝብኝ አደራሽን ማርያም
የአማኑኤል እናት አንቺ መከረኛ
እድሚሽን ጨረስሽው ሆነሽ ሐዘንተኛ
መከራን ያየ ሰው መኟም አይጨክንም
አትጨክኝብኝ አደራሽን ማርያም
← መዝሙር