ድንግል ትንሳኤሽን
✦
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት፪
ሞትን የረገጠው ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል ትንሳኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል

---ሞትማ በሞት ተሸንፏል--
ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል፪-
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት፪
ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል፪-
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት፪
ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተሰወረን የትንሳኤው ምስጢር
በራችንን ዘግተን በጸሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል
ለምን ተሰወረን የትንሳኤው ምስጢር
በራችንን ዘግተን በጸሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል
---ሞትማ በሞት ተሸንፏል--
ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል፪
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት፪
ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል፪
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት፪
መዝሙረኛው አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ሰው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን ባንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሸንፈሽ መቃብር አትወርጂም
ሞትን የማያይ ሰው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን ባንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሸንፈሽ መቃብር አትወርጂም
---ሞትማ በሞት ተሸንፏል--
ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል፪-
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት፪
ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል፪-
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት፪
ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት
ድንግል አሳስቢልን ኪዳነምሕረት