ድንግል ወላዲት ቃል

ድንግል ወላዲተ ቃል
አሟሟትሽ በጥር ነሐሴ መቃብር ድንግል
የአንቺስ ለብቻ ነው ትንሣኤሽ ሲነገር ድንግል
ሥጋሽ በምድር ላይ የታለ እንደ ፍጡር
አርጓል ወደ ሰማይ ከክርስቶስ መንበር
አዝ --------
ሥጋሽን ሲያሳርጉ መላእክት በሰማይ
ቶማስ በደመና ሲመጣ መንገድ ላይ ድንግል
መግነዝ ተቀበለ ለሐዋርያት ሊያሳይ ድንግል
አዝ ----------
ትንሣኤሽን ሽተው ግራ ሲገባቸው ድንግል
ሐዋርያት ጾመው ተገለጥልሻላቸው ድንግል
ተቀብራ አልቀረችው በምድር ከደጇ ድንግል
ወደላይ አረገች እሷም እንደልጇ ድንግል
አዝ -------
ለማየት ሲጓጉ የድንግልን ትንሣኤ ድንግል
እርገቷን አወቁ በብዙ ሱባኤ ድንግል
እኛም እንጸልይ ደጃችን እንዝጋ ድንግል
ከወላዲተ አምላክ እንድናገኝ ዋጋ ድንግል
← መዝሙር