ድንቅ ነው በጣም

ድንቅ ነው በጣም ድንቅ ነው
በሠርጋችሁ እለት ተገኘ መድኃኔዓለም
በሠርጋችሁ እለት ተገኘች ድንግል ማርያም
በቃልህ ተመርተው ለዚህ ቀን በቅተዋል
በፊትህ ጋብቻን ይኸው ፈጽመዋል
በፈሰሰው ደምህ ኅብረት መስርተዋል
በሥጋም በነፍስም የአንተ ነን ብለዋል
አዝ ---
ከአዳም አንድ አጥንት ከጐኑ ወስደህ
አጋር እንድትሆነው ሔዋንን ሰጠህ
ሁለቱንም ባርከህ እንደፈጠርካቸው
ዛሬም ለሙሽሮች ሰላምን ስጣቸው
አዝ ---
ጌታ ሆይ በሕግህ በቃልህ መሠረት
አንድ ሆነዋልና በዚህ ቅዱስ እለት
እርሱንም እሷንም ባርከህ ቀድሳቸው
ዘለዓለማዊ ፍቅር ጽናትን ስጣቸው
አዝ ---
የዲያቢሎስ ተንኮል እንዳያስታቸው
እስከ መጨረሻው ጋሻ ሁንላቸው
ከቅድስቲቷ ቤት ሁለቱም ሳይርቁ
ጽናቱን ስጣቸው አብረው እንዲዘልቁ
← መዝሙር