እግዚአብሔር ፈቅዶ
✦
እግዚአብሔር ፈቅዶ ዛሬ አንድ ሆነናል
እህቴ ሆይ ስሚ ማን ይለያየናል
ሥጋሽ ከሥጋዬ አጥንትሽ ከአጥንቴ
ተዋሕዶአልና ሆነሻል ሕይወቴ፪
በእመብርሃን ምልጃ በጌታ ቸርነት
በቃልህ ከታመንኩ በዚህ ቅዱስ እለት
የአጥንትህ ክፋይ አካልህ ነኝና
ጌታዬ ልበልህ ክብሬ አንተ ነህና፪
አንቺም ተጠበቂ ከዲያብሎስ ሴራ
ሰውነትሽ ዘወትር በጐ ምግባር ይሥራ
ቅድስና ወደሽ ከኃጢአት ራቂ
የሃይማኖትሸን ክር ማእተብሸን አጥብቂ፪
ከቃልህ አልወጣም ጌታዬ ሆይ ስማኝ
እስከመጨረሻው ፍጹም ታዛዥህ ነኝ
በቤተክርስቲያን ጥላ ስር በመሆን
በቃሉ እመራለሁ አንብቤ ወንጌልን፪
እግዚአብሔር ሆይ ስማን ቃልኪዳናችንን
ጋብቻችንን ባርክ ቀድስ ጐጆአችንን
ከዲያብሎስ ሴራ ጠብቀህ እኛን
እስከመጨረሻው በቃልህ አጽናን፪
እህቴ ሆይ ስሚ ማን ይለያየናል
ሥጋሽ ከሥጋዬ አጥንትሽ ከአጥንቴ
ተዋሕዶአልና ሆነሻል ሕይወቴ፪
በእመብርሃን ምልጃ በጌታ ቸርነት
በቃልህ ከታመንኩ በዚህ ቅዱስ እለት
የአጥንትህ ክፋይ አካልህ ነኝና
ጌታዬ ልበልህ ክብሬ አንተ ነህና፪
አንቺም ተጠበቂ ከዲያብሎስ ሴራ
ሰውነትሽ ዘወትር በጐ ምግባር ይሥራ
ቅድስና ወደሽ ከኃጢአት ራቂ
የሃይማኖትሸን ክር ማእተብሸን አጥብቂ፪
ከቃልህ አልወጣም ጌታዬ ሆይ ስማኝ
እስከመጨረሻው ፍጹም ታዛዥህ ነኝ
በቤተክርስቲያን ጥላ ስር በመሆን
በቃሉ እመራለሁ አንብቤ ወንጌልን፪
እግዚአብሔር ሆይ ስማን ቃልኪዳናችንን
ጋብቻችንን ባርክ ቀድስ ጐጆአችንን
ከዲያብሎስ ሴራ ጠብቀህ እኛን
እስከመጨረሻው በቃልህ አጽናን፪
✦