እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው
✦
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው
ስለስምህ እቃጠላለሁ
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል፪
ስለስምህ እቃጠላለሁ
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል፪
ዓለም ሁሉ በጠላኝ ጊዜ
ስንገላታ ይዞኝ ትካዜ
አንተ ከኔ አልተለየህም
እግዚአብሔር ሆይ ወደር የለህም፪
ስንገላታ ይዞኝ ትካዜ
አንተ ከኔ አልተለየህም
እግዚአብሔር ሆይ ወደር የለህም፪
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው
ስለስምህ እዘምራለው
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል፪
ስለስምህ እዘምራለው
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል፪
ሳዖል እኔን ሲያሳድደኝ
ጎልያድም ሲዝትብኝ
ግርማ ሆነህ ከፊቴ የቆምክ
እግዚአብሔር ሆይ ስምህ ይባረክ፪
ጎልያድም ሲዝትብኝ
ግርማ ሆነህ ከፊቴ የቆምክ
እግዚአብሔር ሆይ ስምህ ይባረክ፪
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው
ስለስምህ እዘምራለው
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል፪
ስለስምህ እዘምራለው
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል፪
ሞቷል ብለው ቀብረውኝ ሰዎች
ምስኪን ሆኜ ሳይኖረኝ አንዳች
ከመቃብር ቆፍሮ አወጣኝ
አይዞህ ብሎ አምላክ አጽናናኝ፪
ምስኪን ሆኜ ሳይኖረኝ አንዳች
ከመቃብር ቆፍሮ አወጣኝ
አይዞህ ብሎ አምላክ አጽናናኝ፪
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው
ስለስምህ እዘምራለሁ
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል፪
ስለስምህ እዘምራለሁ
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል፪
ሃሳብህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል
ለዘላለም ያበራልሃል
ታማኝ አባት እርሱ ነውና
ሰላም ይሁን ለሱ ምስጋና፪
ለዘላለም ያበራልሃል
ታማኝ አባት እርሱ ነውና
ሰላም ይሁን ለሱ ምስጋና፪
✦