እግዚአብሔር ሆይ

እግዚአብሔር ሆይ የሚረዳን የለምና
ከኛ አትራቅ ተስፋችን ነህና
አንተን አምነን ስንጠራህ አትለየን
አምላክ ሆይ ጠብቀን
አዝ ---
በአንተ ታምኛለው ዘላለም አልፈር
በጽድቅ ልመራ በፍቅር እንድኖር
ጆሮህን አዘንብልህ ፈጥነህ አድነኝ
መንገዴን አቅንተህ በሕይወት ምራኝ
አዝ ---
አምባና መጠጊያ መሸሸጊያ ሁነኝ
በድካሜ ጊዜ የለም የሚረዳኝ
የእውነት አምላክነህ አቤቱ ተቤዥን
ከአንተ በቀር ለእኛ ምንም ተስፋ የለን
አዝ ---
የሕይወቴ ብርሃን መታመኛዬ ነህ
ዝም አትበለኝ አንተ አቤቱ ስጠራህ
በመከራዬ ቀን አቤቱ ሠውረኝ
በቃልህ እንድኖር በምሕረትህ ጎብኘኝ
አዝ ---
እንዳሽንፍ እርዳኝ የዓለምን ፈተና
ጠላቴ እንዲያፍር በእምነት እንድጸና
አንተ ተዋጋና እንዳልወድቅ እርዳኝ
ከጎኔ አትለየኝ ብርታትን ስጠኝ
አዝ ---
← መዝሙር