እግዚአብሔርን ጠራሁት
✦
እግዚአብሔርን ጠራሁት በኀዘኔ ጊዜ
እግዚአብሔርን ጠራሁት በጭንቀቴ ጊዜ
አወጣኝ ከጭንቀት ከሐዘን ከትካዜ /፪
እግዚአብሔርን ጠራሁት በጭንቀቴ ጊዜ
አወጣኝ ከጭንቀት ከሐዘን ከትካዜ /፪
የልመናዬን ድምጽ እርሱ ሰምቷልና
ጆሮውን ወደ እኔ አዝንብሏልና
በዘመኔ ሁሉ ስጠራው እኖራለሁ
ጎስቋላ ብሆንም ምስጋና አቀርባለሁ፪
ጆሮውን ወደ እኔ አዝንብሏልና
በዘመኔ ሁሉ ስጠራው እኖራለሁ
ጎስቋላ ብሆንም ምስጋና አቀርባለሁ፪
እንደ ቃልህ መጓዝ መራመድ አቅቶኝ
የኃጢአቱ መንገድ ማእበሉ ገፍቶኝ
ወደ እርሱ ስማጸን ደግሞም ስጸጸት
አላሳፈረኝም መጣ በምሕረት ፪
የኃጢአቱ መንገድ ማእበሉ ገፍቶኝ
ወደ እርሱ ስማጸን ደግሞም ስጸጸት
አላሳፈረኝም መጣ በምሕረት ፪
በበዛው ምሕረቱ ያለፈውን ትቶ
በፍቅሩ ጎበኘኝ አልተወኝም ከቶ
ሊቀበኝ ወዶ ፊቱን አበራልኝ
ማን ይቃወመኛል እግዚአብሔር ካለልኝ፪
በፍቅሩ ጎበኘኝ አልተወኝም ከቶ
ሊቀበኝ ወዶ ፊቱን አበራልኝ
ማን ይቃወመኛል እግዚአብሔር ካለልኝ፪
ኖኅን አንዳዳንከው እኛንም አድነን
ከቀስቱ እንድናመልጥ ምልክትን ስጠን
በትርህ ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑን
አንተ ከእኛ ጋር ነህ አንፈራም ክፉውን፪
ከቀስቱ እንድናመልጥ ምልክትን ስጠን
በትርህ ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑን
አንተ ከእኛ ጋር ነህ አንፈራም ክፉውን፪
✦