እልፍ አእላፋት ወትልፊት
✦
እልፍ አእላፋት ወትልፊት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
ኢዮር ራማ ኤረር የመላዕክት ሀገር
የሀይማኖት ፍቅር የምልክት ክር
እውነት የታየብሽ የመላዕክት ክብር
የሀይማኖት ፍቅር የምልክት ክር
እውነት የታየብሽ የመላዕክት ክብር
እልፍ አእላፋት ወትልፊት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
አፅናን ሲል ገብርኤል በአለንበት ቦታ
በሳጥናኤል ነገድ ነበረ ሁካታ
ግማሹ እየካደ ቀሪው ሲያመነታ
በሳጥናኤል ነገድ ነበረ ሁካታ
ግማሹ እየካደ ቀሪው ሲያመነታ
እልፍ አእላፋት ወትልፊት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
የሳጥናኤል ምኞት እንደ አበባ ረግፎ
ሚካኤል ተሾመ በእምነት ተደግፎ
ሳጥናኤል ወደቀ ጸጋውን ተገፎ
ሚካኤል ተሾመ በእምነት ተደግፎ
ሳጥናኤል ወደቀ ጸጋውን ተገፎ
እልፍ አእላፋት ወትልፊት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
ቅዱሳን መላዕክት በእምነት የጸናችሁ
በታላቅ አክብሮት ሰላም እንበላችሁ
ስግደት ዘበፀጋ እንስገድላችሁ
በታላቅ አክብሮት ሰላም እንበላችሁ
ስግደት ዘበፀጋ እንስገድላችሁ
እልፍ አእላፋት ወትልፊት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ፫ አምላክ በማለት
✦