እልል አልል 2

እልል እልል ደስ ይበለን
አጅበን መጣን ሙሽሮቹን
እልል ብላችሁ ተቀበሉን
እናንተ ሙሽሮች እንኳን ደስ አላችሁ
የአብርሃም የሣራ ይሁን ጋብቻችሁ
መልካም መተሣሳብ ክርስቶስ ይስጣችሁ
ሣራና አብርሃም ሁሉም የሚያውቋቸው
ሁለቱም ቅዱሳን ናቸው
ፍቅራቸውን አይቶ አምላክ ባረካቸው
ለእናት ለአባት ታዛዥ ግሩም ልጅ ሠጣቸው
ለጌታ መሥዋእት እኔ ልቅረብ ያለው
ይስሐቅን ለአብርሃም የሠጠው
በመልካም ጋብቻ በጥሩ ትዳር ነው
ቅዱስ አባታችን ፈጣሪያችን ሆይ
ጌታችን አምላካችን ሆይ
በአብርሃም ጎጆ እንደገባህበት 2
በሙሽሮቹም ቤት በረከት ሙላበት
በቃናዋ መንደር የጠራኽ ሠርገኛ
አምላክ ተገኘልህ ሆነህ እድላኛ
በቃናዋ መንደር የጠራሽ ሠርገኛ/2
ድንግል ጎበኘችሽ ሆነሽ እድለኛ
ማርያም ጎበኘችሽ ሆነሽ እድለኛ
← መዝሙር