እልል አማኤል

እልል /6 አማኑኤል ተነሣልን
ደስ ይበልን ሁላችንን
የሲኦል ደጆች ተከፈቱ እልል
የሰይጣንም ሠራዊቶች አፈሩ እልል
በጨለማው ዓለም ተወጠን ሳለን
ጌታ በትንሣኤው ዛሬ አበራልን
አዝ ---
መቃብራት ሁሉ ተከፈቱ እልል
የታሠሩ ነፍሳት ከግዞት ተፈቱ እልል
መግደላዊት ማርያም ትንሣኤውን አይታ
ነገረች ለሐዋርያት በደስታ ተሞልታ
አዝ ---
ሁለቱ መላእክት ብርሃን የለበሱ እልል
ተነሥቷል አሏቸው ሴቶቹ ሲደርሱ እልል
ሐዋርያት አይተው ዜና ትንሣኤውን
አሏአቸው ለድኅነት ሰላም ለእናንተ ይሁን
አዝ ---
← መዝሙር