እልል በሉ
✦
እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
አመስግኑ ለክብሩም ዘምሩለት
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ
በኃጢያት ባርነት ስንኖር ተገዝተን
ከቤቱ ስንርቅ ትእዛዙን አፍርሰን
አይቶ ዝም ላለን ጠላቶቹ ሳለን
ውለታው ግሩም ነው ክብር ለእርሱ ይሁን፪
ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን
ሥጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን
መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም
ምስጋና ይድረሰው ለመድኃኔዓለም፪
ሕይወቱን የሠዋ እንደ አምላክ ማን አለ
ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ
ፍቅሩም አይለካ አያልቅም ቢወራ
ከሰማያት ወርዶ ሆነ ከእኛ ጋር /2
ሥራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን
ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን
ለማይነገረው ለአማላክ ስጦታ
ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ
አመስግኑ ለክብሩም ዘምሩለት
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ
በኃጢያት ባርነት ስንኖር ተገዝተን
ከቤቱ ስንርቅ ትእዛዙን አፍርሰን
አይቶ ዝም ላለን ጠላቶቹ ሳለን
ውለታው ግሩም ነው ክብር ለእርሱ ይሁን፪
ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን
ሥጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን
መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም
ምስጋና ይድረሰው ለመድኃኔዓለም፪
ሕይወቱን የሠዋ እንደ አምላክ ማን አለ
ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ
ፍቅሩም አይለካ አያልቅም ቢወራ
ከሰማያት ወርዶ ሆነ ከእኛ ጋር /2
ሥራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን
ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን
ለማይነገረው ለአማላክ ስጦታ
ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ
✦