እመ አምላክ ሙሽራ ነሽ

እመአምላክ ሙሽራ ነሽ
ለቃል ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ
ኸኸ
12 ዓመት ቤተ መቅደስ የኖርሽ
የመመረጥ ጸጋ ከጌታ ያገኘሽ
አዝ ---
በአብሣሪው መልአክ እጹብ ድንቅ ዜና
ከሰማይ መጣልሽ አቋርጦ ደመና
በ6ኛው ወር ተልኮ ገብርኤል
ቤተመቅደስ ገባ ሊያበስራት ለድንግል
አዝ ---
በልዩ ሰላምታ ሰላም ለኪ አለሽ
የክርስቶስ እናት በጣም ደስ ይበልሽ
መላእክት በሰማይ ያመሰግኑሻል
ክብር ለአምላክ እናት ይድረሳት ይሉሻል
አዝ ---
በማሕፀንሽ ቢያድር የሠራዊት ጌታ
ለመሆን ተመረጥሽ የአምላክ ቅድስት ቦታ
የፈጣሪ እናት መሆንሽን ተረድቶ
ሰላም ላንቺ ይሁን አለሽ እጅ ነሥቶ
አዝ ---
← መዝሙር