እመ አምላክ
✦
እመ አምላክ ፪
አስቢኝ በሠርክ
አስቢኝ በሠርክ
ኀዘኔ ጭንቀቴ በጣም በዛብኝ
ከልጅሽ አማልጅኝ አንቺው አስታርቂኝ
ከመንበሩ ቆመሽ ንገሪው ለልጅሽ
እናቱ ነሽና እሱ አያሳፍርሽ
ከልጅሽ አማልጅኝ አንቺው አስታርቂኝ
ከመንበሩ ቆመሽ ንገሪው ለልጅሽ
እናቱ ነሽና እሱ አያሳፍርሽ
እመ አምላክ ፪ አስቢኝ በሠርክ
እኔ ኃጥያተኛው በደሌን አውቃለው
ምርኩዜ ነሽና እከተልሻለው
መንገዱ ጠፍቶብኝ የጽድቁ ጎዳና
መብራቱን አብሪልኝ እመጣለሁና
ምርኩዜ ነሽና እከተልሻለው
መንገዱ ጠፍቶብኝ የጽድቁ ጎዳና
መብራቱን አብሪልኝ እመጣለሁና
እመ አምላክ ፪ አስቢኝ በሠርክ
መመገብ ይቅርብኝ አልራብምና
ስምሽን ስጠራ እጠግባለውና
አበው ሊቃውንቱ በአንቺ ይመካሉ
እመ አምላክ እያሉ ስምሽን ይጠራሉ
ስምሽን ስጠራ እጠግባለውና
አበው ሊቃውንቱ በአንቺ ይመካሉ
እመ አምላክ እያሉ ስምሽን ይጠራሉ
እመ አምላክ ፪ አስቢኝ በሠርክ
ከገሃነም አውጭኝ ከዚያ ነበልባል
ከሲዖል ወድቄ እንዳልቃጠል
ያ የስቃይ ሀገር ባህሩ ያሰጥመኛል
አንቺ ከለመንሽው ልጅሽ ያዝንልኛል
ከሲዖል ወድቄ እንዳልቃጠል
ያ የስቃይ ሀገር ባህሩ ያሰጥመኛል
አንቺ ከለመንሽው ልጅሽ ያዝንልኛል
እመ አምላክ ፪ አስቢኝ በሠርክ
ወገን አታድርጊኝ ከሲዖል ከተማ
መድረሻ ያሳጣኝ የእሳቱ ጨለማ
አወድሳሸለው በኤፍሬም ውዳሴ
ሁኝልኝ ጠበቃ አደራ ለነፍሴ
መድረሻ ያሳጣኝ የእሳቱ ጨለማ
አወድሳሸለው በኤፍሬም ውዳሴ
ሁኝልኝ ጠበቃ አደራ ለነፍሴ
እመ አምላክ ፪ አስቢኝ በሠርክ
እኔስ እፈራለው ምግባሬን ሳየው
ደካማው እምነቴ እየለየኝ ነው
አልረሳሽም ድንግል እማጸንሻለው
አማላጅነትሸ መድኅን ነው አውቃለው
ደካማው እምነቴ እየለየኝ ነው
አልረሳሽም ድንግል እማጸንሻለው
አማላጅነትሸ መድኅን ነው አውቃለው
እመ አምላክ ፪ አስቢኝ በሠርክ
✦