እመቤታችን ላንቺ

እመቤታችን ላንቺ ስላምታ ይገባሻል
ከሴቶች ሁሉ ተመርጠሻል
ሐርና ወርቁን እያስማማች ስትፈትል
ተዘጋጀላት የመመረጥ እድል
እመቤታችን ------------
እያረጓጓት የሰማይ መላእክት
ቤተ መቅደስ ኖረች አሥራ ሁለት ዓመት
እመቤታችን ላንቺ-------
መንፈስ ቅዱስ እንደቀረባት አውቆ
ሰገደላት ዘካርያስ ታጥቆ
እመቤታችን ላንቺ -------------
መንፈስ ቅዱስ እንደቀረባት አውቃ
ተሳለመቻት ኤልሣቤጥም ታጥቃ
እመቤታችን ላንቺ ---------------
አያስደንቅም ወይ የማርያም ትኅትና
ውኃ ስትቀዳ የአምላክ እናት ሁና
እመቤታችን ላንቺ -----------
የምንጭ ውኃ ምሥጢር የሚያመለክተው
የአምላክ መገኛ ምንጭ እርሷ መሆንዋን ነው
እመቤታችን ላንቺ --------
← መዝሙር