እመቤቴ ማርያም እለምንሻለሁ
✦
እመቤቴ ማርያም እለምንሻለሁ
በለቅሶ በዋይታ ፊትሽ ወድቄያለሁ
እመቤቴ ስሚኝ እለምንሻለሁ፪
ኃዘኔን ጭንቀቴን ለማን እነግራለሁ
ችግሬን ጉዳቴን ለማን አዋያለሁ
እመቤቴ ስሚኝ ተማጽኜሻለሁ፪
ኃዘኑም በዛብኝ ፈተናው ከበደኝ
እንደምን ልቻለው እኔስ ደካማ ነኝ
የአማኑኤል እናት ፈጥነሽ ድረሺልኝ፪
በጥም ተንገዳገድኩ ልወድቅ ነው እኔ
እመ አምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጎኔ
ምንም አጋር የለኝ ካንቺ በቀር ለኔ፪
በለቅሶ በዋይታ ፊትሽ ወድቄያለሁ
እመቤቴ ስሚኝ እለምንሻለሁ፪
ኃዘኔን ጭንቀቴን ለማን እነግራለሁ
ችግሬን ጉዳቴን ለማን አዋያለሁ
እመቤቴ ስሚኝ ተማጽኜሻለሁ፪
ኃዘኑም በዛብኝ ፈተናው ከበደኝ
እንደምን ልቻለው እኔስ ደካማ ነኝ
የአማኑኤል እናት ፈጥነሽ ድረሺልኝ፪
በጥም ተንገዳገድኩ ልወድቅ ነው እኔ
እመ አምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጎኔ
ምንም አጋር የለኝ ካንቺ በቀር ለኔ፪
✦