እመቤቴ ጥላ ከለላዮ

እመቤቴ ጥላ ከለላዬ ረዳቴ የገነት ሙሽራ
የገነት ሙሽራ ማርያም የልዑል ማደሪያ
መጣ በነቢያት ቃለ አብ ተሰብኮ
በስድስተኛው ወር ገብርኤል ተልኮ
ቤተመቅደስ ሳለች ሳለች በፍጹም ት ትና
ደሽ ይበልሽ አላት መልአኩ መጣና
በጥዑም ቃል እርሷን እያጽናና
አዝ ---
እኔ ወንድ ሳላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል
ብላ ጠየቀችው በትኅትና ቃል
ገብርኤልም አላት አትፍሪ ማርያም
እግዚአብሔር ፍጹም ነው የሚሳነው የለም
አዝ ---
መንፈስ ቅዱስ ቀርቦ ይጸልልሻል
የልዑልም ኃይሉ በአንቺ ያድርብሻል
ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ
ይሆናል ዘለዓለም ዓለምን የሚዋጅ
አዝ ---
ይሁንልኝ ብላ ቃሉን ተቀበለች
በፍጹም ተዋሕዶ የአምላክ እናት ሆነች
ድንግል ማርያም በእውነት ልዩነች
አዝ ---
← መዝሙር