እምነት ተስፋ ፍቅር

እምነት ተስፋ ፍቅር ከሌለኝ ለኔ በምድር
/መሥራት ከንቱ ነው ምግባር ትንቢት መናገር ምሥጢር /2
እምነት ከሥራ ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ
/እንደ ሚጮህ ናስ ሆኛለሁ ባዶ ዕቃ
ሆኜ እቀራለሁ/2
ያስታግሣል ፍቅር ያስተዛዝናል ፍቅር
አያቀናናም ፍቅር አያስመካም ፍቅር
አያስታብይም ፍቅር ክፉ አያሠራም ፍቅር
እውነት ይወዳል ፍቅር ዓመፅ ይጠላል ፍቅር
ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬን ከእሳት ብጥል
/ፍቅር ከሌለኝ አይጠቅምም ከዳግም ጥፋት አልድንም
ትንቢትም ቢሆን ይቀራል ልሳንም ቢሆን ይሻራል
/እውቀትም ቢሆን ይጠፋል ጉልበትም ቢሆን ይደክማል /2
እምነት ተስፋ ፍቅር የእነዚህ ሦስቱ ነገር
ጸንተው ይኖራሉ በምድር ከሁሉ በላይ ፍቅር
ከሁሉ በላይ ፍቅር 
← መዝሙር