እናመስግነው

እናመስግነው
አምላካችን ውለታው ብዙ ነው
ከኃጢአት ገደል ከሞት ቤት ጎትቶ
መንግሥቱን ለሰጠን ከሲኦል አውጥቶ
ዘለዓለማዊ ቤት ታላቅ ሀብት ያደለን
መቼም የማይተወን ታላቅ አባት አለን
እናመስግነው
አምላካችን ውለታው ብዙ ነው
ፍጡራን ቢንቁኝ መጎስቆሌን አይተው
ወዳጆች ቢሸሹኝ ተስፋ ቢስ ነው ብለው
እውነተኛው ረዳት አምላኬ መች ተወኝ
ሁለት እጄን ይዞ ልጄ ተነስ አለኝ
እናመስግነው
አምላካችን ውለታው ብዙ ነው
ሞታችንን ሞቶ ሕይወትን ላደለን
ለቸሩ ክርስቶስ ምን እንከፍለዋለን
ለታላቅ ውለታው ጌታ ለዋለልን
በእልልታ እንዘምር በአንድነት ሆነን
← መዝሙር