እናምናለን እኛ
✦
ሐዋርያት አበው እንዳስተማሩን
ስለሰው ልጅ ድኅነት አምላክ ሰው መሆኑን
በስሙ የተጠራን እኛ እናምናለን
መለኮት ከሥጋ ተዋሕዷል ብለን
ስለሰው ልጅ ድኅነት አምላክ ሰው መሆኑን
በስሙ የተጠራን እኛ እናምናለን
መለኮት ከሥጋ ተዋሕዷል ብለን
እናምናለን እኛ ሁለት ልደታትን
የአብ ልጅ ከድንግል ዳግም መወለዱን፪
የአብ ልጅ ከድንግል ዳግም መወለዱን፪
ስግደት የሚገባው የአብ አካላዊ ቃል
ከክቡር ዙፋኑ ከሦስትነት ሳይጎድል
በዚህ ዓለም መጥቶ ሰው ሆኗል ከድንግል
ከአብ አንድነቱ ከቶ ሳይከፈል
አዝ
ቃልም ሥጋ ሆኖ በእኛ ላይ አድሮ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከብሮ
ፍጹም የአምላክ ልጅ ፍጹም ሰውነቱ
ተገልጧል በድንግል በዳግም ልደቱ
አዝ
ከክቡር ዙፋኑ ከሦስትነት ሳይጎድል
በዚህ ዓለም መጥቶ ሰው ሆኗል ከድንግል
ከአብ አንድነቱ ከቶ ሳይከፈል
አዝ
ቃልም ሥጋ ሆኖ በእኛ ላይ አድሮ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከብሮ
ፍጹም የአምላክ ልጅ ፍጹም ሰውነቱ
ተገልጧል በድንግል በዳግም ልደቱ
አዝ
✦