እናት አለኝ የምታብስ እንባ

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለው ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት
አንባ መጠጊያ ናት
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቆቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደ እኔ ቀርበሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነ ምህረት
አንባ መጠጊያ ናት
አዝ........
ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ድስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
አዝ ..........
ከጥፋቱ ውሀ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በህይወት አለው ጥልቁን ተሸግሬ
አዝ ...........
በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
← መዝሙር