እናታችን ጽዮን

እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምስጋና
መጠጊያ ማረፊያ ጥላችን ነሽና
ከገነት ብንወጣ ማረፊያ ሆንሽን
የምሕረት ደመና ውኃ ሰጠሸን
የሕይወት እንጀራ አመጣሽልን
በአሥራትም በአደራ ለአንቺ ተሰጠን
አዝ . . .
የኤልሳቤጥ አጽናኝ የጭንቅ ቀን ደራሽ
የኃጢአ ችን ብዛት ዳገት ሳይሆንብሽ
ምሥራችን ደስ ይዘሽልን መጣሽ
ማርያም ስንልሽ ደረሽልን ፈጥነሽ
አዝ . . .
ውለ ሽ ብዙ ነው ከልብ የማይጠፋ
ስምሽ መጽናኛ ነው አዝኖ ለተከፋ
በእንተ ማርያም ብሎ ለለመነ
የሰማይ የምድሩም ማንም አልጨከነ
አዝ . . .
በትራችን አንቺ ነሽ የምትደግፊን
ባሕረ እሳትን የም ሳልፊን
ጽርሐ ሥላሴ ነሽ ማ ደረ መለኮት
ሁል ጊዜ አንጠግብሽም እንላለን ብጽእት
አዝ . . .
← መዝሙር