እንደ በደሌ

እንደ በደሌ
ሊቀ.መዘ ቴዎድሮስ ዮሴፍ
===========
እንደበደሌ አልከፈልከኝ
ፍቅር ነህና እያለፍከኝ
ምን እከፍላለሁ ላንተ የሚሆን
ታቀው የለም ወይ ችሎታዬን
አዝ---------------//
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል
ታርቀዋለህ የኔን በደል
እንደምትወደኝ አቃለሁ እኔ
ባስመርርህም በእድሜ ዘመኔ
አዝ-------------//
ከሰው ሁሉ ጋር ብትፈራረድ
የትኛው ይሆን ፀድቆ የሚሄድ
የአለምን ሐጥያት ደምህ ሸፈነው
የተፈወስኩት እኔም በእርሱ ነው
አዝ------------------//
ዘመኔ እንደ ሳር መሆኑን አስብ
እድሜዬ ታጥሯል በግዜ ገደብ
መልካም ሰርቼ እንዲያልፍ ወራቴ
በጎውን አብዛ በሰውነቴ
አዝ-------------------//
የልጅነቴን አታስብብኝ
መጨረሻዬን አሳምርልኝ
በሩን አትዝጋው የአዳራሹን
ዘይቴን ልሙላ የመቅረዙን
← መዝሙር