እንደ እግዚአብሔር ያለ
✦
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለምና
እልል በሉ ቁሙ ለምስጋና፪
አዝ ---
ባሕር ተከፈለ እሲኪታይ መሬቱ
ፈርኦን ወደቀ አልሠራም ትምክህቱ
ደካሞቹም ጸንተው ተራመዱ
ኃይለኞቹም ይኸው ተዋረዱ
አዝ ---
የኢያረኮ ቅጥር የማይደፈረው
ይኸው ፈራረሰ የሰው እጅ ሳይነካው
ኃይለኞቹም ቢበረታቱብን
እንጸናለን በእርሱ ተደግፈን
አዝ ---
የተወረወረው የጠላታችን ጦር
ሜዳ ላይ ወደቀ ጋሻ ሆኖ እግዚአብሔር
ለሥላሴ ይድረስ ምስጋናችን
ተሸነፈ አዳኝ ጠላታችን
አዝ ---
ባሕር ላይ ሲራመድ ሞገስ አለው እርሱ
በግርማው ሲነሳ ጸጥ ይላል ነፋሱ
የድንግል ልጅ እኛ የምናመልከው
ከሀሊ ነው የለም የሚሳነው
እልል በሉ ቁሙ ለምስጋና፪
አዝ ---
ባሕር ተከፈለ እሲኪታይ መሬቱ
ፈርኦን ወደቀ አልሠራም ትምክህቱ
ደካሞቹም ጸንተው ተራመዱ
ኃይለኞቹም ይኸው ተዋረዱ
አዝ ---
የኢያረኮ ቅጥር የማይደፈረው
ይኸው ፈራረሰ የሰው እጅ ሳይነካው
ኃይለኞቹም ቢበረታቱብን
እንጸናለን በእርሱ ተደግፈን
አዝ ---
የተወረወረው የጠላታችን ጦር
ሜዳ ላይ ወደቀ ጋሻ ሆኖ እግዚአብሔር
ለሥላሴ ይድረስ ምስጋናችን
ተሸነፈ አዳኝ ጠላታችን
አዝ ---
ባሕር ላይ ሲራመድ ሞገስ አለው እርሱ
በግርማው ሲነሳ ጸጥ ይላል ነፋሱ
የድንግል ልጅ እኛ የምናመልከው
ከሀሊ ነው የለም የሚሳነው
✦