እንደቸርነትህ
✦
እንደቸርነትህ አቤቱ ማረን ፪
አንደምሕረትህ ይቅርታን ስጠን ፪
ከኃጢአቴም አንጻኝ ከክፉ በደሌ ፪
ለዚያች ክፉ ኃጢአት እንዳልሆናት ሎሌ ፪
እኔም አመጻዬን በደሌን ሳውቀው ፪
ፍጹም የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው ፪
አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረግሁ ፪
አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቅሁ ፪
ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን ፪
መውደቄን ተመልከት አምላክ ብርሃን ፪
አሁን ተባርክ ዘንድ ማህበራችንን ሀገራችንን
ጌታ ሆይ ላክልን መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስን
አንደምሕረትህ ይቅርታን ስጠን ፪
ከኃጢአቴም አንጻኝ ከክፉ በደሌ ፪
ለዚያች ክፉ ኃጢአት እንዳልሆናት ሎሌ ፪
እኔም አመጻዬን በደሌን ሳውቀው ፪
ፍጹም የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው ፪
አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረግሁ ፪
አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቅሁ ፪
ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን ፪
መውደቄን ተመልከት አምላክ ብርሃን ፪
አሁን ተባርክ ዘንድ ማህበራችንን ሀገራችንን
ጌታ ሆይ ላክልን መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስን
✦