እንደተቆጣኝ
✦
እንደተቆጣኝ አልቀረም በርኅራኄ@ው ማረኝ
ቁጣውን መልሶ ለነፍሴ ለልቤ መጽናኛ ሰጠኝ
ምን ልክፈለው ለአምላክ ለወደደኝ
ልስገድለት ላመስግነው ኃይል ይስጠኝ፪
ዳገት ቁልቁለት በዛብኝ ለጽድቅ ወደአንተ ስጓዝ
ጠላት ተጠምጥሞ ከአንገቴ ጎንጎኔን ነደፈኝ በመርዝ
መፍትሔው< ጠፋብኝ ስቃይ በዛብኝ
አምላኬ ሆይ በጥበብህ አላቀኝ ፪
ብቻኛ ነኝ ጭንቅ የያዘኝ የጠበበኝ
የዓለም ነፋስ ማእበሉ ያንገላ ኝ
መላም የለኝ እኔ ተክዤ ቆሜአለሁ
ኃይሌ ጉልበቴ መድኃኒቴ በለኝ አለሁ፪
ቆሜ ሳየው ፊት ኀእላዬን ቀኝ ግራዬን
ረዳት የለኝ ምርኩዝ የለኝ ነኝ ብቻዬን
የውስጥ የውጭውን ዘርዝሬ የምነግረው
እንደነፍሴ የምቆጥረው የማዋየው፪
አይተህ ይህን መጨነቄን መገፋቴን
ላክልኝ ለኔ ድንግልን እመቤቴን
ቅዱሳን ሰማእ ት ጻድቃን መላዕክትን
ፍጥረትህ ነኝ እንዳልጠፋ አትጨከን ፪
የነበርክ ያለክ ለዘለዓለም የምትኖር
ከሥራዬ ባሳዝንህ ዘወትር
ያለረዳት አጽናኝ ብቻዬን ያልተውከኝ
ተስፋ አልቆርጥም ላመሰግንህ ፍቀድልኝ፪
ቁጣውን መልሶ ለነፍሴ ለልቤ መጽናኛ ሰጠኝ
ምን ልክፈለው ለአምላክ ለወደደኝ
ልስገድለት ላመስግነው ኃይል ይስጠኝ፪
ዳገት ቁልቁለት በዛብኝ ለጽድቅ ወደአንተ ስጓዝ
ጠላት ተጠምጥሞ ከአንገቴ ጎንጎኔን ነደፈኝ በመርዝ
መፍትሔው< ጠፋብኝ ስቃይ በዛብኝ
አምላኬ ሆይ በጥበብህ አላቀኝ ፪
ብቻኛ ነኝ ጭንቅ የያዘኝ የጠበበኝ
የዓለም ነፋስ ማእበሉ ያንገላ ኝ
መላም የለኝ እኔ ተክዤ ቆሜአለሁ
ኃይሌ ጉልበቴ መድኃኒቴ በለኝ አለሁ፪
ቆሜ ሳየው ፊት ኀእላዬን ቀኝ ግራዬን
ረዳት የለኝ ምርኩዝ የለኝ ነኝ ብቻዬን
የውስጥ የውጭውን ዘርዝሬ የምነግረው
እንደነፍሴ የምቆጥረው የማዋየው፪
አይተህ ይህን መጨነቄን መገፋቴን
ላክልኝ ለኔ ድንግልን እመቤቴን
ቅዱሳን ሰማእ ት ጻድቃን መላዕክትን
ፍጥረትህ ነኝ እንዳልጠፋ አትጨከን ፪
የነበርክ ያለክ ለዘለዓለም የምትኖር
ከሥራዬ ባሳዝንህ ዘወትር
ያለረዳት አጽናኝ ብቻዬን ያልተውከኝ
ተስፋ አልቆርጥም ላመሰግንህ ፍቀድልኝ፪
✦