እንዲህ አለው ጴጥሮስ

እንዲህ አለው ጴጥሮስ ኢየሱስን
ምሥጢር ገሃድ ሲሆን በዚያ በተራራ
በአንድ ላይ እንኑር ሦስት ዳስ እንሥራ
አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ
ተለወጠ ገፁ ከመ ጽጌሬዳ
ወርዶ ከለላቸው ደመና ጸዓዳ
አዝ.....
ከሰማይ ቃል መጣ እንደዚህ የሚል
የምወደው ልጄ እርሱን ስሙት ሲል
አዝ…..
ኤልያስም ሔደ በሠረገላው
ሙሴም ከመቃብር ወደ መኖሪያው
አዝ…..
ስላስደነቃቸው ግሩም ተአምራቱ
ይህን ምሥጢር አይተው ተሰነባበቱ
አዝ…..
← መዝሙር