እንዲህ አለው ጵጥሮስ
✦
እንዲህ አለው ጰ?ጥሮስ ኢየሱስን
ምሥጢር ገሃድ ሲሆን በዚያ በተራራ
ባንድ ላይ እንኑር ሦስት ዳስ እንስራ
አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ
ተለወጠ ገጹ ከመ ጽጌሬዳ
ወርዶ ከለላቸው ደመና ጸዓዳ
ከሰማይ ቃል መጣ እንደዚህ የሚል
የምወደው ልጄ እርሱን ስሙት ሲል
ኤልያስም ሄደ በሰረገላው
ሙሴም ከመቃብር ወደ መኖሪያው
ስለአስደነቃቸው ግሩም ተአምራቱ
ይህን ምሥጢር አይተው ተሰነባበቱ
ምሥጢር ገሃድ ሲሆን በዚያ በተራራ
ባንድ ላይ እንኑር ሦስት ዳስ እንስራ
አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ
ተለወጠ ገጹ ከመ ጽጌሬዳ
ወርዶ ከለላቸው ደመና ጸዓዳ
ከሰማይ ቃል መጣ እንደዚህ የሚል
የምወደው ልጄ እርሱን ስሙት ሲል
ኤልያስም ሄደ በሰረገላው
ሙሴም ከመቃብር ወደ መኖሪያው
ስለአስደነቃቸው ግሩም ተአምራቱ
ይህን ምሥጢር አይተው ተሰነባበቱ
✦