እንዲህ እናምናለን እንታመናለን

እንዲህ እናምናለን እንታመናለን
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር
ብለን
--------------- --------
የእግዚአብሔር አብ ፍቅሩ ይሰፋል ይረቃል
ልጁን እስኪሰጠን እንዲሁ ወዶናል
በደብረ ታቦር ላይ እርሱን ስሙት ላለው
በመዝሙር ለቃኘን ምስጋና ይድረሰው
…አዝ…
አብርሃም ይስሐቅን አባት እንደሆነው
አይደለም ልደቱ በአማን ልዩ ነው
የተወለደ ነው ከቶ አልተፈጠረም
ከአባቱ ጋራ ቅድመ ዓለም የኖረው
…አዝ…
ሊያጽናናን የሚላክ ከአብ የሚወጣው
በሃምሳኛው ዕለት ወደኛ የመጣው
የራሱ የሆነ ፍጹም አካል ያለው
ጰራቅሊጦስ ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ነው
የራሱ የሆነ ፍጹም አካል ያለው
ጰራቅሊጦስ ጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
…አዝ…
በእደ ዮሃንስ ሲጠመቅ በማይ
ወልደ አምላክ መሆኑ ስንሰማ ከላይ
በአምሳለ እርግብ ወርዶ በርሱ የኖረው
ለአካላዊው ቃል እስትንፋስ ሕይወት ነው
← መዝሙር