እኔ አንተ ቤት
✦
እኔ አንተ ቤት
እኔ አንተ ቤት እኔ አንተ ፊት
የምቆም ሠው አይደለሁም
ግን ፍቅር ነህ ለዘለዓለም
የሚመስልህ ማንም የለም፪
የምቆም ሠው አይደለሁም
ግን ፍቅር ነህ ለዘለዓለም
የሚመስልህ ማንም የለም፪
ፀሎቴ ቢሆን ለወረት ጎዶሎ ቢሆን የኔ እምነት
ባረከኝ እኔን ከሠማይ በደል ጥፋቴንም ሳታይ
ቀባኸኝ ጠርተኸኝ ከዱረ ሠጠኸኝ ከፍ ያለ ወንበር
ሳይኖረኝ አንድም በጎነት ባረከኝ በእጅህ በረከት
ባረከኝ እኔን ከሠማይ በደል ጥፋቴንም ሳታይ
ቀባኸኝ ጠርተኸኝ ከዱረ ሠጠኸኝ ከፍ ያለ ወንበር
ሳይኖረኝ አንድም በጎነት ባረከኝ በእጅህ በረከት
አዝ___
ቃልኪዳንህን አክባሪ ታማኝ ነህ ሁሌም መሀሪ
የማልከውንም መሀላ አትረሣም አትልም ችላ
መካሪ ድንቅ መምህሬ ላንተ ነው ዜማ መዝሙሬ
ፍቅር ነህ ከአባትም በላይ የሠማይ የምድር ሢሣይ
የማልከውንም መሀላ አትረሣም አትልም ችላ
መካሪ ድንቅ መምህሬ ላንተ ነው ዜማ መዝሙሬ
ፍቅር ነህ ከአባትም በላይ የሠማይ የምድር ሢሣይ
አዝ___
መሻቴን ብቻ ስላየህ ደካማ ልጅክን ጎበኘህ
ብቃቴ መቼ ሆነና ያቆመኝ ላንተ ምስጋና
አንኳኩ ስላልክ አንኳኳው ጠይቁ ስላልክ ጠየኩኝ
ከፍተሃል በርህን ለኔ የታተምኩብህ መድህኔ
ብቃቴ መቼ ሆነና ያቆመኝ ላንተ ምስጋና
አንኳኩ ስላልክ አንኳኳው ጠይቁ ስላልክ ጠየኩኝ
ከፍተሃል በርህን ለኔ የታተምኩብህ መድህኔ
✦