እኔ እወድሀለው

እኔ እወድሀለው መድኃኒቴ
መታመኛዬ ነህና ረዳቴ መታመኛዬ
መመኪያዬ አንተ ነህ የህይወቴ ተስፋ
ጌታ ሆይ ጠብቀኝ ከሰይጣን ዘለፋ
አቤቱ ጌታ ሆይ በስምህ አዳነኝ
ጩኸቴንም አዳምጥ ጸሎቴንም ስማኝ
የነፍሴ መዳኛ የአጥንቴም ሕይወቱ
ወልደ አብ ክርስቶስ አንተ ነህ በእወነቱ
ወደኔ ተመልክት ነፍሴም አድናት
እንደቸርነጥ ሰውረኝ ከሀጢአት
ከአንተ ተለይቼ እንዳልጠፋብህ
የቀናውን መንገድ ይምራኝ መንፈሽ
ወደዓለም ስትመጣ በግርማ በክብር
ጌታ ሆይ ጠብቀኝ ወድቄ እንዳልቀር
← መዝሙር