እኔስ በምግባሬ
✦
እኔስ በምግባሬ ደካማ ሆኛለሁ
እዘኝልኝ ድንግል እለምንሻለሁ ፪
እዘኝልኝ ድንግል እለምንሻለሁ ፪
ያንን የእሳት ባሕር እንዳላይ አደራ
ድረሽልኝ ድንግል ስምሽን ስጠራ ፪
ድረሽልኝ ድንግል ስምሽን ስጠራ ፪
የዳዊት መሰንቆ የኤልያስ መና
የናሆም መጽኃኒት ነይ በደመና፪
የናሆም መጽኃኒት ነይ በደመና፪
አንቺ ነሽ ጉልበቴ በደከመኝ ጊዜ
የልቤ መጽናኛ ረዳት ምርኩዜ ፪
የልቤ መጽናኛ ረዳት ምርኩዜ ፪
አፈሳለሁ እንባ በጣም ተጨንቄ
እማጸንሻለሁ በደሌን አውቄ፪
እማጸንሻለሁ በደሌን አውቄ፪
✦