እርግብና ዋኔን

እርግብና ዋኔን ---- ዋኔን --- አብሮ ዘመቱና ---ዋኔን
እርግብ ደህና ገባች ---ዋኔን -ዋኔን ገደሉና -- ዋኔን (አዝ)
አዝ-----
በዘርና ጎሣ ዋኔን
ሰው ሁሉ ተከፍሎ ዋኔን
ሰይፍንም ጨበጠ ዋኔን
ልቦናው ቂም አዝሎ ዋኔን
ሠላምን የሚያወርድ ዋኔን
አንድ የሚያረገን ዋኔን
እባክህን አምላክ ዋኔን
ሙሴን አድለን ዋኔን
ሠላምህን አብዛ
ምድሪቷን አስባርክ
የቅዱሳን አምላክ
በጭንቃችን ድረስ
አዝ-----
በወገን ላይ ወገን ዋኔን
ይብቃ መነሳት ዋኔን
ይስፈን በምድር ላይ ዋኔን
የእግዚአብሔር መንግስቱ ዋኔን
ኖራችን ይሰቀል ዋኔን
እንያዝ በገና ዋኔን
ሰላም እናግኝ ዋኔን
በፍቅር እንጽና ዋኔን
ምድሪቷን አሳርፍ
ሠላምህም ይብዛ
በአንድነት አኑረን
የዓለሙ ቤዛ
አዝ-----
የመርገም ጨርቅ ሆነ ዋኔን
ጽድቃችን በሙሉ ዋኔን
አንተን ያልበደለ ዋኔን
ማነው በዘመኑ ዋኔን
አማነው በማታ ዋኔን
ቀን ያከበርነውን ዋኔን
የእኛ ሥራ ሆኗል ዋኔን
መክሰስ የበታውን ዋኔን
ፍቅር ባትሆን ኖሮ
በያቅትህ መጥላት
አይታይም ነበር
የሰው ልጅ በሕይወት
አዝ-----
እርግብና ዋኔን ---- ዋኔን --- አብሮ ዘመቱና ---ዋኔን
እርግብ ደህና ገባች ---ዋኔን -ዋኔን ገደሉና -- ዋኔን
← መዝሙር