እርስታችን ነሽ
✦
እርስታችን ነሽ እንወርስሻለን
ከምድርሽ ወይንን እንለቅማለን
ይትረፈረፋል ፅዋችን ሞልቶ
አንችን ይዘናል አናፍርም ከቶ
❖ ❖ ❖
የእንጀራ ምድር የፍቅር ሀገር
የለንም ወገን ካ'ንቺ በስተቀር
በአክአብ መሬት የማንቀይርሽ
ደጅሽ ቆመናል ጎብኝን በእጆችሽ
✥ ✥ ✥
ዳዊት አባትሽ እንዳለው ፤ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ
በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ
✟ ✟ ✟
ወደ ምድራችን መርቶን ስንገባ
አንችን አገኘን ታላቋን መባ
የህይወት ውሃ ፈልቋል ከሆድሽ
እንዳንጠማ ዳግም ልጆችሽ
✥ ✥ ✥
ነዶው በዛልን የስንዴው ዛላ
ወይኑን ብንጨምቀው ፅዋችን ሞላ
መሆንሽን አውቀን የበረከት ምድር
አንጠፋም ድንግል ከመቅደስሽ ስር
✝ ✝ ✝
አሁን በደስታ ስፍራ ይዘናል
መስቀል ላይ ሆኖ ጌታ ሰጥቶናል
ከዝ'ች እርስት ሚነቅለን የለም
አትሞበታል የደሙን ማህተም
ከምድርሽ ወይንን እንለቅማለን
ይትረፈረፋል ፅዋችን ሞልቶ
አንችን ይዘናል አናፍርም ከቶ
❖ ❖ ❖
የእንጀራ ምድር የፍቅር ሀገር
የለንም ወገን ካ'ንቺ በስተቀር
በአክአብ መሬት የማንቀይርሽ
ደጅሽ ቆመናል ጎብኝን በእጆችሽ
✥ ✥ ✥
ዳዊት አባትሽ እንዳለው ፤ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ
በልቤ ላይ ነግሰሻል ምልጃሽ እየጠበቀኝ
✟ ✟ ✟
ወደ ምድራችን መርቶን ስንገባ
አንችን አገኘን ታላቋን መባ
የህይወት ውሃ ፈልቋል ከሆድሽ
እንዳንጠማ ዳግም ልጆችሽ
✥ ✥ ✥
ነዶው በዛልን የስንዴው ዛላ
ወይኑን ብንጨምቀው ፅዋችን ሞላ
መሆንሽን አውቀን የበረከት ምድር
አንጠፋም ድንግል ከመቅደስሽ ስር
✝ ✝ ✝
አሁን በደስታ ስፍራ ይዘናል
መስቀል ላይ ሆኖ ጌታ ሰጥቶናል
ከዝ'ች እርስት ሚነቅለን የለም
አትሞበታል የደሙን ማህተም
✦