እርሱ ባይወለድ

እርሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
ቸር አባታችን እሰይ እሰይ
እርሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
መድኃኒታችን እሰይ እሰይ
መች ትገኝ ነበረ እሰይ እሰይ
ገነት ምድራችን እሰይ እሰይ
አዝ ------
እሰይ እሰይ ተወለደ
ከሰማያት ሰማይ ወረደ
ከድንግል ማርያም ተወለደ
አዝ -----------
እንደጠል ወረደ እሰይ እሰይ
ከሰማይ ወደእኛ እሰይ እሰይ
ወገኖቹን ሊያድን እሰይ እሰይ
ከኃጢአት ቁራኛ እሰይ እሰይ
አዝ ---------------
እሰይ እሰይ
ብርሃን ወጣላቸው እሰይ እሰይ
ለእምነት ወገኖቹ እሰይ እሰይ
በጨለማ ጉዞ እሰይ እሰይ
እንዲያ ሲሰላቹ እሰይ እሰይ
እሰይ እሰይ -------------
እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ
አንድያ ልጁን እሰይ እሰይ
እርሱ ወድዷልና እሰይ እሰይ
እንዲሁ ዓለሙን እሰይ እሰይ
እሰይ እሰይ ---------------
← መዝሙር