እሰይ ተወለደ
✦
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት ፫
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት፫
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት፫
ትንቢት ተናገሩ ነቢያቱ ሁሉ፫
አምላክ ቀዳማዊ ይመጣል እያሉ፫
አምላክ ቀዳማዊ ይመጣል እያሉ፫
ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ፫
የእስራኤል ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ
የእስራኤል ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ
ሰብአ ሰገል መጡ ይዘው እጅ መንሻ ፫
ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው፫
ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው፫
ሕፃናት እንሂድ ከልደቱ ቤት፫
ውኃው ሆኗልና ማርና ወተት፫
ውኃው ሆኗልና ማርና ወተት፫
✦