እስከ መቼ ነው

እስከ መቼ ነው የማልለወጠው
ባልተሰበረ ልብ የምመላለሰው
በሰጠኸኝ ጸጋ ድካሜ ተከድኖ
ዓለም ይክበኛል አልቆና አግኖ
ይህን ከንቱ ወጥመድ ጣለው ከኋላዬ
ትንሽ ሰው መሆኔን ይወቅ ህሊናዬ
አዝ ---
ፀሐይ ስትቀላ ከዋክብት ሲረግፉ
ለገናናው ክብርህ ወድቀው ሲሸነፉ
ለሁለት ሲከፈል ድንጋያማው አለት
የእኔ ልብ መቼ ይሆን የሚሸነፍለት
ቃልህን ስስማ ልቤን ይነካኛል
ጽታቅን አስባለሁ ሐዘን ይሰማኛል
ወዲያው ተመልሼ ሁሉን እረሳለሁ
ለዚህ ዓለም ስብከት ልቤን እከፍታለሁ
← መዝሙር