እስኪላግንሽ
✦
እስኪ ላግንሽ እመቤቴ ማርያም
እስቲ ላድንቅሽ ንጽሕት ቅድስት ማርያም
መመኪያ ርስቴ ነሽና እናቴ ፪
አዝ------------------------
አዛኝት ማርያም ክብርሽ ልዩ ነው
ለተቸገረ ስምሽ ስንቅ ነው
መደኃኒቴ ነሽ እጠራሻለው
ከእግርሽ ወድቄ እሰግድልሻለው
አዝ ---------------------
የኤዶም ወንዝ የገናት ፈሳሽ
ምክንያተ ድኅነት ሰው የዳነብሽ
ንጹሑን በግ ጌታን ያስገኘሽ
አብርሃም ያየሽ እፀ ሣቤቅ ነሽ
አዝ ----------
እያሽበሽብኩ ልዘምርልሽ
ልዝረፍ ቅኔውን ነይ ላወድስሽ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ምስጋና አንቺ ነሽ
ዳዊት በመዝሙር የዘመረልሽ
አዝ -------
አእላፍ መላእክት ዙሪያሽን ከበው
ሲያመሰግኑሽ በሰማይ ያየው
እፁብ ድንቅ ነው ግሩም ተአምር
ዘርዝሬ አልጨርስ ያንቺን ክብር
አዝ---------
እስቲ ላድንቅሽ ንጽሕት ቅድስት ማርያም
መመኪያ ርስቴ ነሽና እናቴ ፪
አዝ------------------------
አዛኝት ማርያም ክብርሽ ልዩ ነው
ለተቸገረ ስምሽ ስንቅ ነው
መደኃኒቴ ነሽ እጠራሻለው
ከእግርሽ ወድቄ እሰግድልሻለው
አዝ ---------------------
የኤዶም ወንዝ የገናት ፈሳሽ
ምክንያተ ድኅነት ሰው የዳነብሽ
ንጹሑን በግ ጌታን ያስገኘሽ
አብርሃም ያየሽ እፀ ሣቤቅ ነሽ
አዝ ----------
እያሽበሽብኩ ልዘምርልሽ
ልዝረፍ ቅኔውን ነይ ላወድስሽ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ምስጋና አንቺ ነሽ
ዳዊት በመዝሙር የዘመረልሽ
አዝ -------
አእላፍ መላእክት ዙሪያሽን ከበው
ሲያመሰግኑሽ በሰማይ ያየው
እፁብ ድንቅ ነው ግሩም ተአምር
ዘርዝሬ አልጨርስ ያንቺን ክብር
አዝ---------
✦