እስመ አልቦ ነገር
✦
እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
አልቦ ነገር ፫ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
አልቦ ነገር ፫ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
መካኒቱን ወላድ አንተ ታደርጋለህ
ከጭንጫ ዐለት ላይ ውኃን ታፈልቃለህ
በወጀብ መካከል አንተ መንገድ አለህ
የአስጨናቂዎችን ክንድ ትሰብራለህ
ከጭንጫ ዐለት ላይ ውኃን ታፈልቃለህ
በወጀብ መካከል አንተ መንገድ አለህ
የአስጨናቂዎችን ክንድ ትሰብራለህ
እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
አልቦ ነገር ፫ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
አልቦ ነገር ፫ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
ለሶምሶን ብርታቱን የሰጠኸው ፅናት
በጠላቶቹ ፊት ሞገስ የሆንክለት
የእጅህን በረከት ከአርያም ላክልኝ
ፊትህን አብራልኝ እኔም እድናለሁኝ
በጠላቶቹ ፊት ሞገስ የሆንክለት
የእጅህን በረከት ከአርያም ላክልኝ
ፊትህን አብራልኝ እኔም እድናለሁኝ
እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
አልቦ ነገር ፫ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
አልቦ ነገር ፫ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
የኤርትራ ባሕር ከፊት ተዘርግቶ
የፈርኦን ሠራዊት ከኋላቸው መጥቶ
ዋይታ ሲበረታ ሙሴን ተናገርከው
ባሕር ተከፈለ ሕዝቡን አሻገርከው
የፈርኦን ሠራዊት ከኋላቸው መጥቶ
ዋይታ ሲበረታ ሙሴን ተናገርከው
ባሕር ተከፈለ ሕዝቡን አሻገርከው
እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
አልቦ ነገር ፫ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
አልቦ ነገር ፫ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር
ሰማያት ደመናን ከቶ ባይቋጥሩ
ከብቶችም ከበረት ከጋጣ ባይኖሩ
ሸለቆን በውኃ ቤትን በበረከት
መሙላት ያውቅበታል የዘለዓለም አባት
ከብቶችም ከበረት ከጋጣ ባይኖሩ
ሸለቆን በውኃ ቤትን በበረከት
መሙላት ያውቅበታል የዘለዓለም አባት
✦