እስመ ለዓለም ምሕረቱ

እስመ ለዓለም ምሕረቱ
አያልቅም ብዙ ነው የአምላክ ቸርነቱ
አመሰገኑት ጌታን ሁላችሁ በአንድነት
መሐሪ ነውና ለሰው ልጆች ሕይወት
የማይሞተው ሞቶ የተቀበረው
በእሳተ ገሃነም እኛን ሊያድን ነው
ከማርያም የነሣው ያ ቅዱስ ሥጋው
በመስቀል ላይ ሲውል የሚያሳዝነው ነው
በፈጠረው ፍጥረት ለሕማም ተሰጥቶ
ነፍሳትን አወጣ ከሲኦል ጎትቶ
ዘማሪ ተምሮ ማስተማር
← መዝሙር